የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ኮርፖሬሽን አዲስ አመራሮች፣ ከፓርኩ ነዋሪዎች ጋር የመጀመሪያ የሆነ የትውውቅና የውይይት መድረክ አካሂደዋል። ይህ በዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ በለጠ እሱባለው እና በምክትላቸው አቶ ኦላና አበበ የተመራው መድረክ፣ አመራሮቹ አልሚ ድርጅቶች በይፋ ለመተዋወቅና የነዋሪዎችን ሀሳብ ለመስማት ያለመ ነበር።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አልሚ ድርጅቶች የፓርኩን ጠንካራ ጎኖች በመጠቆም እንዲሁም መስተካከል አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች በማንሳት ለአዲሶቹ አመራሮች ግብዓት ሰጥተዋል። አልሚ ድርጅቶቹ ያነሷቸውን ሀሳቦችና አስተያየቶች ተከትሎ፣ አመራሮቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አከለዉም “ይህ የትውውቅ መድረክ የመጀመሪያችን ነው” በማለት አንዳንድ ጉዳዮችን በጠባብ መድረኮች ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ የሚፈቱ ጉዳዮች እንደሚኖሩም ገልጸዋል። በመጨረሻም በተነሱት ችግሮች ላይ ተጨባጭ መፍትሄ ለማምጣት ከአልሚ ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ሁሉም የፓርኩ አልሚ ድርጅቶች ለስነ-ምህዳሩ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል።

